አርባምንጭ፣ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም፡- የአርባ ምንጭ ክላስተር ያዘጋጀው የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የጋሞ ዞን ዋና ዞን አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) የቴክኒክና ዘርፍ በሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ብቁና በሙያ የሚተማመን ዜጋ በመፍጠርና ድህነትን በመቀነስ ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እውን ለማድረግ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም መሆኑን ተናግረዋል ።
የደቡብ ኢትዮጰያ ክልላዊ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በዛብህ ገበየሁ በጋራ እንደ ብሩህ አዕምሮና እንደ ሰለጠነ ዜጋ ዕድገትን የመንዳት፣ እንዱስትሪዎችን የመቀየር፣ እና ቴክኖሎጂዎችን ለበጎ መሳሪያ የምንጠቀም ኃይል መሆን እንደሚገባ የገለጹት አቶ በዛብህ ለተወዳዳሪዎቾ መልካም ዕድል ተመኝተዋል ።
የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኮሌጅ ዲንና የክላስተር ኮሌጆቹ አስተባባሪ አቶ በዛብህ በርዛ ብርቱና ጤናማ ፉክክር በተወዳዳሪዎች መካካል በመፍጠር በየደረጃው ለሚካሄደው ውድድር ጠንካራ ተሳታፊዎችን እና ተወካዮችን እንዲመለመሉ በማድረግ የተቋማትንና የተወዳዳሪዎች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የውድድሩ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።
“ብሩህ አዕምሮዎች ፤የተፍታቱ እጆችና በክህሎት የበቁ ዜጎች በሚል መሪ ቃል በክላስተር ኮሌጆች የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በሁነቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች እና እንግዶች እንዲሁም ተወዳዳሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ይህ ሁነትም ከዛሬ ጀምሮ ለጉብኚዎች ክፍት በመሆኑ መጎብኘት የሚፈልጉ አካላት መጥተው እንዲጎበኙ የክላስተር ኮሌጆቹ አስተባባሪ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በውድድሩ ላይ አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች እንየደረጃቸው የማበረታቻ ሽልማት እደተዘጋጀላቸውና በውድድሩ የሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎችም ክላስተሩን በመወከል ለክልላዊ ውድድር እንደሚሳተፍ ተገልጿል፡፡
1. የውድድሩ ዓላማ
- ተማሪዎች በሙያዊ ክህሎቶች፣ ቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ምርምር ውጤቶች የሚወዳደሩበት መድረክ ማቅረብ።
- ብቃት ያላቸው ዜጎችን በማፋጠን ለአገር ልማት አስተዋፅኦ ማድረግ።
2. ተሳታፊዎች እና እንግዶች
- በውድድሩ ላይ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)፣ የክልል እና የዞን ባለስልጣናት፣ አሰልጣኞች፣ ተማሪዎች እና እንግዶች ተገኝተዋል።
3. የቀረቡ ስራዎች
- የፋሽን ሾው (Fashion Show) – የልብስ ዲዛይን ማሳየት።
- የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች – ተማሪዎች የሚያቀርቡት አዳዲስ ምርቶች ወይም ስልተ-ቀመሮች።
- ሌሎች የሥራ ክህሎት ማሳያዎች – ችሎታዎች , ኤግዚቢሽን።
4. ለአገር ጠቀሜታ
- ይህ ውድድር የሀገራችንን የቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ እድገት ለማፋጠን የሚያስችል አስፈላጊ መድረክ ነው።
- ተማሪዎች በተግባራዊ ክህሎቶች እንዲበለጥጡ እና ለስራ ገበያ እንዲዘጋጁ ያግዛል።




