ህዳር 25/2017 ዓ.ም የአርባምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት የHIV (ኤች.አይ.ቪ) ቀን በአለምአቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ግዜ፣ በአገርአቀፍ ደረጃ ለ36ኛ ዙር እንዲሁም በክልላችን ደቡብ ኢ/ያ ለ 2ኛ ግዜ እና በኮሌጃችን ለ36ኛ ግዜ “ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች.አይ.ቪ አገልግሎት ለሁሉም” “Take the rights path” በሚል መሪቃል እየተከበረ ይገኛል። በመርሐግብሩ የተገኙት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ በዛብህ ባርዛ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሁሉም ሰው ለአፍታ እንኳን ሳይዘናጋ እራሱንና ሌሎችንም ጭምር በትኩረት መጠበቅና መተላለፊያ መንገዶችን ለይቶ በመረዳት የተለመደውን ቅድመጥንቃቄ መደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።