የአርባምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ዛሬ ማለትም በቀን 29/02/2017 ዓ.ም በኮሌጁ መሰብሰቢያ አዳራሽ አጠቃላይ ሰራተኞችን ያሳተፈ ስብሰባ አካሂዷል። በመሆኑም በእለቱ አጠቃላይ የኮሌጁ ሰራተኞች የ2016 ዓ.ም የ12 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የማቅረብ መርሐግብር የተከናወነ ሲሆን እንዲሁም በቀጣይ በ2017 ዓ.ም የሚኖረውን የስራ ትግበራ እቅድ እና የዞኒግና ዲፍሬንሼሽን ስትራቴጂ አተገባበር ላይ ገለጻና ስብሰባን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በስብሰባው እየተነሱ ያሉ እጅግ ብዙ ጉዳዮች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል
የዞኒግና ዲፍሬንሼሽን በተመለከተ የተፈቀዱ የት/ት መስኮች፦
1, Mechanical
2, Machining
3, Hotel & Tourism.
4, Garment
5, Furniture Making
6, Agro Processing ናቸው።
እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫ ያልሆኑ ነገርግን በልዩ ፍላጎቶች የተጨመሩ
7, ICT
8, Biomedical
9, Power
መሆናቸው በኮሌጁ ዋና ዲን አቶ በዛብህ ባርዛ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለጻ ተሰጥቶበት የስብሰባው ተሳታፊዎች ሀሳብ በማንሸራሸር ውይይት ተካሂዷል።