አርባምንጭ የካቲት 27/2017 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን ፦  በቴክኖሎጂው ዘርፍ  በተደረገ  ውድድር  በሀገር አቀፍ እና በክልል 1ኛ  ብሎም በአፍሪካ ደረጃ 4ኛ ለወጡ ቴክኖሎጂስቶች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የጋሞዞ ምክትል አስተዳዳሪና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መኮንን ቶንቼ  በቴክኖሎጂው ዘርፍ  በተደረገ  ውድድር  በክልል ፣ በሀገር አቀፍና በአፍሪካ  ደረጃ በተደረገው  ውድድር  ላስመዘገቡት  ውጤት  እውቅና ተሰጥተዋል ።

በቀጣይም የተሰሩትን ቴክኖሎጂዎች ለህብረተሰቡ በማድረስ የህብረተሰቡን የዕለተ እለት እንቅስቃሴ  ማቅለል ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩም ምክትል አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

ቴክኖሎጂስቶች  አከባቢው የሚታወቅበትን የሽመና ጥበብ ለሀገር ለማስተማወቅ የሽመና ማዳወሪያ ማሽን ለውድድሩ  ይዘው በመቅረብ ማሸነፋቸውም ተመላክቷል።

የዞኑ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት  ሥልጠና  መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡቶ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና  ኮሌጅ  የዜጎችን አዳጊና ተለዋዋጭ  የገበያ ፍላጎት  መሠረት  በማድረግ ብቁ፣ የተነቃቃና ከወቅታዊ  ሁኔታዎች  ጋር አዛምዶ የህብረተሰቡን  ችግር የሚፈታ ቴክኖሎጂ    በማቅረብ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ እረገድ ጉልህ ሚና እየተወጣ ይገኛል  ብለዋል።

አክለው የዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት  ሥልጠና  መምሪያ  በቴክኖሎጂው ዘርፍ  በተደረገ  ውድድር  በሀገር አቀፍ እና በክልል 1ኛ  ብሎም በአፍሪካ ደረጃ 4ኛ ወጥተው ማሸነፍቸውን አስታውሰው በ2017 በሚደረገው ክልል ና ሀገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ፣ የክህሎትና ምርምር ውድድር እራሳቸውን እንዲያዘጋጁም አሳስበዋል ።

በመድረኩ ከቴክኖሎጂው መነሻ እስከ ፈጠራ ስራው ያለውን  ሂደት  ለታዳሚው የተብራራ ሲሆን በመረሃ ግብሩ ማጠቃለያም ለቴክኖሎጂስቶቹ  የእውቅና  ሴርቴፍኬት እና የገንዘብ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ::