በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በተባበሩት መንግስታት ተቋማት የሚደገፍ ዞኖችና ወረዳዎች ሁለተኛ ዙር የ lBEX, PIM እና HACT ሥልጠና በአርባ ምንጭ ከተማ  አርባምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት VDI smart lab ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል። በስልጠናው ከ7 ዞኖች 12 ወረዳዎች  የተውጣጡ የበጀትና ሂሳብ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ስልጠናው ቀደም ሲል በዎላይታ ሶዶ_ ዩኒቨርስቲ ከ2 ዞኖች ለተውጣጡ ባለሙያዎች መሠጠቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን  3ኛ ዙር  ለተቀሩት 3 ዞኖች በተመሳሳይ መንገድ ሥልጠናው ተጠናክሮ ቀጥሏል።